Logo
News Photo

የሀዘን መግለጫ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ዶ/ር ያሬድ ዩኒቨርሲቲያችንን ከመጋቢት 10 2010 እስከ ታህሳስ 30 2012 ዓ/ም ለሁለት አመታት በፕሬዝዳንትነት መርተዋል። 

ዶ/ር ያሬድ ዩኒቨርሲቲያችንን በከፍተኛ አመራርነት ከማገልገላቸውም በላይ ህይወታቸው እስካለፈበት ነሐሴ 11 2017 ዓ/ም በመምህርነት እና በከፍተኛ ተመራማሪነት አገልግለዋል። 

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በቀድሞ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለ ዶ/ር ያሬድ ማሞ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል።

Share This News

Comment