Logo
News Photo

የሐዘን መግለጫ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ ጉግሳ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። 

ዶ/ር ሲሳይ ጉግሳ በኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ከመምህርነት ጀምሮ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን በመሆን ተቋማችንን እና ሀገራቸውን በታላቅ ቅንነት ከማገልገላቸውም በላይ በርካታ ተማሪዎችን እስተምረው ለወግ ማእረግ ያበቁ ምሁር ነበሩ። 

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በዛሬው እለት ሁለት እንቁ ምሁራኖቹን በማጣቱ የተሰማው ሀዘን ጥልቅ መሆኑን እየገለፀ ለዶ/ር ሲሳይ ጉግሳ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እና ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል።

Share This News

Comment