Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሳሙና እና በረኪና ምርት ያሰለጠናቸውን 100 ወጣቶች አስመረቀ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከሀረርጌ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር ለ100 ወጣቶች የሳሙና እና በረኪና አመራረት ስልጠና በመስጠት ዛሬ አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው በተለይ ከወጣቶች ስራ ፈጠራ እና ክህሎት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ክፍተቶችን ክግንዛቤ በማስገባት ስልጠናውን መስጠቱ ተነግሯል። 

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በምርቃት ስነ-ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ መጠን ተግባር ተኮር አጫጭር ስልጠናዎች በማዘጋጀት ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን ባለሙያ እያቀረበ መሆኑን አመልክተዋል። መሰል ስልጠናዎች ወጣቶች በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ተቀጥረው እንዲሰሩ ከማስቻሉም በላይ በግል እና በቡድን ተደራጅተው በመስራት የራሳቸን ገቢ ማመንጨት እንዲችሉ እገዛ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም አክለውም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ወጣቶችን ከማስልጠን በተጨማሪ የሰለጠኑ ወጣቶች ገበያ ውስጥ የሚያጋጥማቸን ተግዳሮች በመከታተል እና ድጋፍ በማድረግ ለወጣቶቹ ስኬት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። 

በሀረጌ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የኢፋ ፕሮጀክት ዋና ተጠሪ ወ/ሮ ጺዮን ነጋ በበኩላቸው ተቋማቸው በተለይ ሴቶች እና ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገን የጠቆሙ ሲሆን ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሌሎች ስልጠናዎችን እንደሚያዘጋጁ ተናግረዋል።

Share This News

Comment