Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል የክረምት በጎ ፈቃድ ህክምና በአስተዳደሩ የገጠር ወረዳዎች በመገኘት አገልግሎት ሰጠ

በድሬዳዋ አስተዳደር ገጠር ማህበረሰብ በዋሂል ወረዳ፣ ሁሉም ጤና ባለሞያዎችን በሳተፍ  የክረምት በጎ ፈቃድ ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል።

ሆስፒታሉ በድሬዳዋ ከተማ የተለያዩ ኣካባቢዎች በመዘዋወር አንዲሁም ጊዜያዊ የምርመራ ጣቢያዎችን በማዘጋጀት በርካታ ነዋሪዎችን ተደራሽ ያደረገ የህክምና ምርመራ አና የምክር አገልግሎት አየሰጠ ሲሆን ይህንኑ አገልግሎት ለገጠሩ ማህበረሰብም መስጠት ጀምሯል። ሆስፒታሉ በቀጣይም ሌሎች አካባቢውችንም ተደራሽ በማድረግ የጤና አገልግሎት አንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆሲፒታል የክረምት በጎ ፈቃድ የህክምና አገልግሎት በመስጠት በሃገር ደረጃ ተሸላሚ ተቋም እንደሆነ ይታወቃል።


Share This News

Comment