Logo
News Photo

የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ኮሌጆች አና ዳይሬክተሮች አውቅና ሰጠ

በ2017 የትምህርት ዘመን የተሻለ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ኮሌጆች አና ዳይሬክተሮች እውቅና ተሰጥቷል። የተሰጠው እውቅና በአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ዘርፍ ስር ያሉ ቢሮዎች እና ሰራተኞችን ለማበረታት አንዲሁም የተሻለ የስራ ተነሳሽነትን ለመፍጠር በማሰብ መሆኑ ተጠቁማል።
በእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በስሩ የሚገኙ ዲን አና ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤቶች በበጀት ዓመቱ ለሰሯቸው ስራዎች ሁሉ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ድክመት የተስተዋለባቸውን አንዳንድ ተግባራት በጋራ ለማረም እና ለውጥ ለማምጣት አንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።
የእለቱ የክብር አንግዳ አና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ነስረዲን ተማም አንደተናገሩት ‘’የተቋም ስኬት በሰራተኞች ጥረት አና ኣመራሮች ጥንካሬ የሚወሰን መሆኑን’’ ጠቁመው ‘’የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በበጀት ዓመቱ ላሳካቸው ስኬቶች ሁሉ ሁሉም ቢሮዎች አና አመራሮቻቸው ድካም አና ልፋት በመሆኑ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል። መሰል የእውቅና መርሃ ግብሮች ሰራተኞችን ለበለጠ መነሳሳት የሚረዳ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል አንደሚገባ ዶ/ር ነስረዲን ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ ለሁሉም ኮሌጆች እና ዳይሬቶሬቶች እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ 3 ኮሌጆች እና ዳይሬቶሬቶች ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።

Share This News

Comment