የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ''Regional Labour Migration Knowledge Hub'' ዋና መቀመጫ እና አስተባባሪ እንዲሆን ተመረጠ።
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ለሚያቋቁሙት እና ትኩረቱን በስደት ላይ አድርጎ የሚሰራ ''ማዕከል'' ዋና አስተባባሪ እንዲሆን ተመረጠ። ዩኒቨርሲቲው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በማዘጋጀት እና አጋር አካላትን በማስተባበር ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማበርከቱ ከ 8 ሀገራት የተውጣጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያቋቋሙትን ማዕከል የማስተባበር እና የመምራት እድል እንዲሰጠው አስችሏል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ተፅእኖ መፍጠር በሚያስችሉ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ የዩንቨርሲቲውን ራዕይ እውን ለማድረግ እየሰራ ስለመሆኑ የተጠቆመ ሲሆን የምስራቅ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች እና ተወካዮቻቸው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ የተሳካ ሆኖ እዲጠናቀቅ ላበረከተው አስተዋፅዖ እና ኮንፍረንሱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ላደረገው መስተንግዶ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
Share This News