የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ550 አቅመ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡
ዩኒቨርሲቲው የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶቹን በ13 የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩ እና አቅመ ደካማ ተማሪዎች ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የተደረገው የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ 550 ደርዘን ደብተር ፣ 100
የደብተር መያ ቦርሳዎች እና 100
የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም ) ናቸው፡፡
ድጋፉን ለትምህርት ቤቶቹ ያበረከቱት በዩኒቨርሲቲው ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል ''የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር እና ምርምር ዙሪያ ከሚሰራቸው በርካታ ስራዎች ባሻገር አቅመ ድካሞችን ማዕከል ያደረገ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁ ሲሆን መሰል ማህበረሰብ ተኮር የድጋፍ ስራዎችን ቀጣይነት ባለው መልኩ እና ሰፊ የማህበረሰቡን ክፍል ባሳተፈ መልኩ አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት ገልፀዋል።
የማኅበረሰብ አገልግልት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ወንዲፍራው ደጀኔ በበኩላቸው በትምህርት መርጃ ቁሳቁስ አለመኖር ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ታስቦ የተደረገ ድጋፍ ነው ብለዋል።የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግልት ስራዎች በከተማና በገጠር ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ህንፃ እድሳት፣ ቤተ-መፅሐፍት የማደረጃት ሥራ እና የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን በመለገስ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
Share This News