Logo
News Photo

የ”Kudu Accelerator” ፕሮግራም የማስተዋወቂያ መድረክ በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት Ignite Investment እና GFA በተሰኘ የጀርመን ግብረሰናይ ድርጅት የሚደገፍ እና በስራ ላይ ያሉ ጀማሪ ቢዝነሶችን የሚያግዝ Kudu Accelerator ፕሮግራምን የሚያስዋውቅ መድረክ በድሬዳዋ ተካሂዷል፡፡

በማስተዋወቂያ ፕሮግራሙ ላይ ከድሬዳዋ አስተዳደር የተውጣጡ እና ከሁለት አመት በላይ በስራ ላይ የቆዩ ጀማሪ ስታርታፕ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዞች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት እና የግል ተቋማት ተወካዮች፣ እንዲሁም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ተገኝተዋል። በማስታወቂያ መድረኩ ላይ ሰፋ ያለ ገለፃ Ignite Investment እና GFA በተወከሉ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን ከተሳታፊዎች አና ባለ ድርሻ አካላት ጋርም ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

Accelerator ፕሮግራም ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ስታርታፕ ቢዝነሶች መሳተፍ እንደሚችሉ የተጠቆመ ሲሆን ፕሮግራሙ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለአምስት ወራት የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል፡

 

Share This News

Comment