ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች በ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና በ 2018 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን
እና አስተዳደር
ሰራተኞች በ2017 በጀት ዓመት እቅድ
አፈጻጸም እና በ 2018 በጀት ዓመት
እቅድ ዙሪያ ሰፊ
ውይይት አደረጉ። በውይይቱ
የተቋሙ አጠቃላይ የስራ
አፈጻጸም፣ ቀጣይ ዓመታዊ
እቅድ እና የለውጥ ስራዎች ምንነት
እና እንደ
ተቋም የተሰሩ ስራዎች
ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በዚሁ
የውይይት መድረክ ላይ
በመገኘት የዩኒቨርሲቲውን የ2017
በጀት ዓመት እቅድ
አፈጻጸም በሁለት አውዶች
ማለትም ተቋሙ ከትምህርት
ሚኒስቴር የተሰጡትን ቁልፍ
ውጤት አመላካቾች በተመለከተ
እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው በበጀት
ዓመቱ ያቀዳቸን እቅድ
አፈጻጸሞች ለይተው አቅርበዋል።
ዩኒቨርሲቲው በተለይ ከምርምር፣
ቴክኖሎጂ ፈጠራ እና
ስርጭት፣ በማህበረሰብ ተሳትፎ
እና ማህበራዊ
ሃላፊነቶችን ከመወጣት አንጻር፣
ዓለማቀፋዊነት እና ዓለም አቀፍ ጉድኝት
ስራዎች፣ ተቋማዊ አስተዳደር
እና አመራርን
በተመለከተ የተሰሩ ስራዎችን፣
ምቹ የስራ
አካባቢን ከመፍጠር አንፃር
የተሰሩ ስራዎችን በሰፊው
ያቀረቡ ሲሆን በ
4 ግቦች እና 25 ዝርዝር ተግባራት የተደራጀውን
የዩኒቨርሲቲውን ዓመታዊ እቅድ
አፈፃፀምንም ለተቋሙ ሰራተኞች
አቅርበዋል።
በውይይት መድረኩ ዩኒቨርሲቲው
በ2018 በጀት
ዓመት ያቀዳቸውን እቅዶች
እና በተቋማዊ
ለውጥ ምንነት እና
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከለውጥ
ስራዎች አንፃር እየሰራ
ያለውን ተግባራት ለሰራተኛው
ቀርቧል።
ከመድረክ የቀረቡትን ሰነዶች
መሰረት በማድረግ ከተሳታፊዎች
ጥያቄ እና አስተያየቶች የተሰጠ ሲሆን
ዩኒቨርሲቲው በተለይ በ2017
ዓ/ም
ለከወናቸው አፈፃፀሞች ምስጋና
በማቅረብ ወደፊት ሊሻሻሉ
ስለሚገባቸው ጉዳዮች፣ ትኩረት
ተሰጥቶ ሊሰራባቸው ስለሚሹ
ስራዎች ከቤቱ ሀሳብ
ቀርቦ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
ከሰራተኞች ለቀረቡ ጥያቄዎች
ምላሽ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው
ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም
ሰራተኞች በ2017 የበጀት ዓመት ለተመዘገበው
ተቋማዊ ስኬት ትልቁን
ድርሻ እንደሚወስዱ በመጠቆም
የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን
ከማስቀጠል እንዲሁም ውስንነቶችን
ከማሻሻል አንፃር ሁሉም
የዩኒቨርሲቲው አመራር እና
ሰራተኛ ከመቼው ጊዜ
በተለየ ትጋት ሊሰራ
ይገባዋል’’
ሲሉ ተናግረዋል።
ለውጥ ለማምጣት የተቋሙ
ሰራተኞችን ጥረት ይፈልጋል
ያሉት ዶ/ር ኡባህ ሁሉም
ሰራተኛ ወደ ተቋሙ ሲመጣ ሊሰራ
ስለሚገባው እና በየእለቱ ስለሚከውነው ተግባር
አስቀድሞ አቅዶ እና
አስቦ ሊሆን እንደሚገባ
አሳስበዋል። የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
በተለይ የመሰረተ ልማት
ግንባታ፣ ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር
አኳያ እና የመማር ማስተማር እንዲሁም
የምርምር ስራዎችን በተሻለ
ጥራት እና ልህቀት ከመፈፀም አንፃር
በርካታ ስራዎችን እየሰራ
መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት
ጠቁመዋል።
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
ልየታ እና የትኩረት አቅጣጫ ጋር
ተያይዞ ስለሚነሱ ጉዳዮች
አስተያየት የሰጡት ዶ/ር ኡባህ ‘’ሁሉም ትምህርት ክፍሎች
ከኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር በመፍጠር፣ ስርዓተ
ትምህርቶቻቸውን ኢንዱስትሪው ከሚፈልገው
እና ጊዜው
ከሚጠይቀው እውቀት እና
ክህሎት አንፃር በመቃኘት
ተወዳዳሪ የመሆን ግዴታ
ያለባቸውን መሆኑን በመጠቆም
ትምህርት ክፍሎች የራሳቸውን
የቤት ስራ በአግባቡ በመወጣት ቅድሚያ
እራሳቸውን ተወዳዳሪ እና
ተመራጭ ማድረግ ይኖርባቸዋል’’ ብለዋል።
በእለቱ ከሰራተኞች ለተነሱ
ገንቢ አስተያየት እና
ጥያቄዎች የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዝዳንቶች ምላሽ
በመስጠት የእለቱ መድረክ
ፍፃሜውን አግኝቷል።
Share This News