የዩኒቨርሲቲው መማክርት (Council) በ2018 በጀት አመት ቁልፍ ውጤት አመላካቾች ዙሪያ ውይይት አካሄደ
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ 2018 በጀት አመት የሚከወኑ 100 ቁልፍ ተግባራት ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስምምነት የፈጸመ ሲሆን የስምምነቱን ቁልፍ ተግባራት እና መለኪያዎች ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው መማክርት (Council) ጋር ውይይት አድርጓል።
ውይይቱ በየደረጃው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲውን አመራር ያሳተፈ ሲሆን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስምምነት የተደረሰባቸው ቁልፍ ውጤት አመላካች እና ተግባራት በዩኒቨርሲቲው የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ላመስግን አየለ አማካኝነት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ውይይቱን የመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በዚሁ ወቅት አንደተናገሩት ‘’ ትምህርት ክፍሎችን፣ ቤተሙከራዎች አና ሰርቶ ማሳያ ማአከላትን በሀገር አቀፍ አና አለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አንዲያገኙ ማስቻል፣ የትኩረት መስክን አና አካባቢያዊ ፀጋን መሰረት አድርጎ የልህቀት ማዕከላትን ማደራጀት፣ ትክክለኛ መረጃን በወቅቱ የማድረስ፣ ቅይጥ የበይነ መረብ ትምህርቶችን በስፋት የመስጠት፣ ማህበረሰብ አቀፍ የልማት አና ሰብዓዊ ድጋፍቾን በሰፊው የመስራት አንዲሁም ጭብጥ ተኮር ምርምሮችን ከአጋር አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ዩኒቨርሲቲው አቅዷል’’ ያሉ ሲሆን ለእቅዱ ስኬት ሁሉም የተቋሙ ሰራተኛ በንቃት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ዛሬ የተደረገውን የመማክርት ስብሰባ ተከትሎ ሁሉም አመራር የሚመለከተውን ቁልፍ ተግባራት ቆርሶ በመውሰድ ለተግባራቱ ተፈ ፃሚነት በስሩ ከሚገኙ የስራ ክፍሎች ጋር የሚፈራረም ሲሆን የስራ ክፍሎች ደግሞ በስራቸው ከሚገኙ እያንዳንዱ መምህራን አና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር የሚፈራረሙ ይሆናል።
Share This News