የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በቅርቡ ስራ የጀመረውን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ትምህርት ቤት ጎበኙ
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አሊዪ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በቅርቡ ሥራ የጀመረውን የሁለተኛ ደረጃ ሞዴል ትምህርት ቤት ዛሬ ጎብኝተዋል።
ኃላፊው በቆይታቸው ወቅት የመማሪያ ክፍሎችን ተዘዋውረው በመመልከት የመማር ማስተማር ሂደቱ የተመለከቱ ሲሆን ከተማሪዎች ጋር በቀጥታ በመገናኘትም የማበረታቻ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ሱልጣን በዚሁ ወቅት ለተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት "ይህንን ታሪካዊ ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ጊዜያችሁን ለትምህርት ብቻ በማዋልና በትጋት በማጥናት ለውጤት መብቃት አለባችሁ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጥራት ያለው ትምህርትን ለህብረተሰቡ ለማድረስ እንዲሁም እንደ ሀገር በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ላይ እየተሰራ ያለውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት ለማገዝ በማሰብ ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የከፈተ ሲሆን ለትምህርት ቤቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በሟሟላት ሙሉ የመማር ማስተማር ስራ አስጀምሯል።
Share This News