የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከምክትል ፕሬዝዳንቶች እና በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ስር ከሚገኙ ስራ አስፈጻሚዎች እና ዳይሬክተሮች ጋር በቁልፍ ወጤት አመላካቾች (KPI) ዙሪያ የኮንትራት ስምምነት ፈፀሙ
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ 2018 በጀት አመት ሊተገብሩ በታቀዱ እና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተደርሶባቸው የተላኩ ቁልፍ የውጤት አመላካች ተግባራቶች ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ ዘርፎች እና አመራሮቻቸው ጋር የስራ ውል ስምምነት ተደርጓል፡፡
ስምነቱ በተለይ ከትምህርት ሚኒስቴር የተላኩ ቁልፍ ውጤት አመላካች ተግባራትን በባለቤትነት የሚወስዱ ፈፃሚ የስራ ክፍሎችን በመለየት፣ ለእቅዶቹ ተግባራዊነት አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ አንዲሁም የስራ ክፈሎችን አፈፃፀም መነሻ በማድረግ እውቅና ለመስጠት እንዲሁም ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሚረዳ ተጠቁሟል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳነት ዶ/ር ኡባህ አደም በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ሁሉም የስራ ክፍሎች የሚመለከታቸውን ስራዎች ቆርስው በመወሰድ እና ለስራው ተፈፃሚነት የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አክለውም የተቋሙ ስኬት ሁሉም የስራ ክፍል በሚያስመዘግበው ጥረት እና ስኬት የሚገለፅ በመሆኑ በተለይ ተሸጋሪ ስራዎችን በመረዳዳት እና በመደጋገፍ መንፈስ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በቁልፍ ወጤት አመላካቾች ዙሪያ የኮንትራት ስምምነት የፈረሙት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በስራቸው ከሚገኙ ዳይሬክተሮች፣ ዲኖች እና ቡድን መሪዎች የሚፈራረሙ ሲሆን ስምምነት ሂደቱ በቀጣይነት ከሁሉመ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ ጋር የሚፈፀም መሆኑ ተመላክቷል፡፡
Share This News