በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ኢንኩቤሽን ማዕከል ምሩቃን የበለፀገ መተግበሪያ ተመረቀ
Saba Booking የተሰኘ እና በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ኢንኩቤሽን ማዕከል የቀድሞ ምሩቃን የተሰራ መተግበሪያ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡ መተግበሪያው ቱሪስቶች እና ወደ ድሬዳዋ፣ ሐረር እና ጅግጅጋ ከተማ በእንግድነት የሚመጡ እንገዶች ካሉበት ቦታ ሆነው የሆቴል እና መሰል አገልገሎቶችን እንዲያኙ የሚረዳ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ባደጉት ሀገራት የቱሪዝም ሴክተሩ በመሰል ቴክኖሎጂዎች እንደሚደገፍ በመጠቆም ለሀገራችን ቱሪዝም አገልግሎት ጥራት እና ለሴክተሩ መነቃቃት አገልግሎትን የሚያዘምኑ መሰል ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ያስፈልጋል በማለት ተናግረዋል፡፡ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ኢንኩቤሽን ማዕከል ምሩቃን የሆኑት ተማሪዎች ለሰሩት ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ ምስጋና ያቀረቡት ዶ/ር ኡባህ ዩኒቨርሲቲው ማዕከሉ እንዲጠናከር በማድረግ እና ወደ ማዕከሉ ለሚገቡ ወጣቶች ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል
Saba Booking በድሬዳዋ፣ ሐረር እና ጅግጅጋ ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን ተደራሽነት የሚያረጋግጥ፣ የክልሎቹን ባህላዊ እሴቶች እና የቱሪስት መስህቦች በማስተዋወቅ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶችን ቁጥር እንዲጨምር የሚያግዝ እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን በከተማ አስተዳደር ደረጃ የተጀመሩ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎች ላይም የራሱን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተነግሯል፡፡
ቴክኖሎጂውን ያበለፀጉ ተማሪዎች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በመርሃ ግብሩ ይፋ ያደረጉ ሲሆን ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
Link: https://www.instagram.com/sababooking/
Share This News