Logo
News Photo

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛው ዙር የተጠናቀቁ የምርምር ስራዎች የቀረቡበት ግምገማዊ መድረክ ተካሄደ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ባዘጋጀው የተጠናቀቁ የምርምር ስራዎች መገምገሚያ መድረክ ላይ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ተወካይ ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንዳሉት በዩኒቨርሲቲው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዬች ላይ ትኩረት ያደረጉ የጥናትና የምርመር ስራዎች በብዛትም ሆነ በጥራት እየተካሄዱ መሆናቸውን ገልፀው እነዚን የምርምር ስራዎች ወደ ተግባር በመቀየር የማህበረሰቡን ችግር መፍታት እንዲችሉ ከፍተኛ ጥረት  ይጠይቃል ብለዋል፡፡  

 ዶ/ር መገርሳ አክለውም በግምገማዊ መድረኩ ላይ የሚቀርቡት የተጠናቀቁት የምርምር ስራዎች በአፋጣኝ ወደ ተግባር ተቀይረው የማህበረሰቡን ችግሮች በዘላቂነት መፍታት እንዲችሉ ሁሉም አካል የበኩሉን ርብርብ ያደርግ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡  

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ጉዳዮች ዳሬክቶሬት አዘጋጅንት ለሁለት ቀን በቆየው ግምገማዊ መድረክ ላይ 28 የተጠናቀቁ የምረምር ስራዎች ቀርበው በመድረኩ ተሳታፊዎች ግምገማ ተደርጎባቸዋል፡፡

Share This News

Comment