ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች አቀበባበል እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራር ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ደማቅ አቀባበል አደረገ፡፡ በመድረኩ ዩኒቨርሲቲው ስለሚሰጠው የቅድመ ምረቃ ፕሮገራሞች፣ ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች፣ የሬጅስትራር አገልግሎቶች፣ የምዝገባ እና ክትትል እንዲሁምተማሪዎች ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ስነምግባሮች እና ደንቦች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረገጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ‘’የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን መርጣችሁ፣ ከቅርብም ከሩቅም የሀገራችን ክፍሎች የመጣችሁ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ ሁለተኛ ቤታችሁ በሰላም መጣችሁ’’ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪን ፍላጎት ያማከለ አገልግሎት እንዲሁም ጊዜው የሚዋጅ የትምህርት ዘዴን በመተግበር ሰፊ ስራ እየሰራ ምሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ኡባህ አደም ‘’የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተሳካ የትምህርት ቆይታ እንዲኖራችሁ ከዛሬዋ እለት ጀምሮ ተመርቃችሁ ከዚህ ዩኒቨርሲቲ በስኬት እስክትወጡ አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ ያደርጋል’ በማለት ተናግረዋል፡፡
በእለቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ባህላዊ ውዝዋዜ እና ኪነት ቡድን ጥዑመ ዜማ እና ውዝዋዜ በማቅረብ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን አዝናንተዋል፡፡
Share This News