ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በጋራ ለመስራት ተስማሙ
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በጥራት ፍተሻና ሰሬተፍኬሼን አገልግሎት፣ የላብራቶሪ አክሪዲቴሽንና የሰው ሃይል ልማት እንዲሁም ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ዶ/ር ፍሬው ምትኩና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርመርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ተማም አወል ፈርመዋል፡፡ በዚሁ ወቅት የቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ቤካ ተገኝተው ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ በጋራ ሊሰሯቸው ስለሚገቡ ጉዳዮች ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በቀጣይነትመ ተቋማቱ የጋራ ስራዎችን ለማቀድና የወደፊት አቅጫን ለመንደፍ የሚያስችል የጋራ ግብረ ኃይል ለማቋቋም እና በሁለቱም ተቋማት ያለውን አስቻይ ሁንታዎች ባገናዘበ መልኩ አቅዶ ለመስራት በመስማማት የእለቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡
Share This News