Logo
News Photo

የአዕምሮ ጤና ቀን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡

የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ12ኛ ጊዜ  በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብራል ፡፡

ይህንን አስመልክቶ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን በፓናሉ መክፈቻ ላይ በዩኒቨርሲቲው የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡ ም/ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ‘’በአሁኑ ሰዓት የአዕምሮ ጤና ችግር በማኅበረሰባችን ላይ እያስከተለ ያለው አሉታዊ ጫና ለመቀነስ የሁሉም ወገንን ርብርብር ይፈልጋል’’ ብለዋል፡፡

በተለይም የአዕምሮ ጤና ችግር እንደ ድሬደዋ እያስከተለ ያለውን ችግር ለመፍታት ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በጠቆም ዩኒቨርሲቲው በአዕምሮ ጤና ዙሪያ የሚሰራቸውን የማህበረሰብ አገልግሎቶች አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የዘንድሮው የአዕምሮ ጤና ቀን "የአዕምሮ ጤና አገልግሎትን በድንገተኛ እና ከፍተኛ አደጋ ወቅት ተደራሽ እናድርግ" በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም ጥናታዊ ፅሁፎችን መሰረት ያደረጉ ሰፊ የፓናል ውይይት በማድረግ ተከብሯል፡፡ 

ዓለም አቀፍ የአዕምሮ ጤና ቀን በየዓመቱ እ.ኤ.አ ጥቅምት 10 የሚከበር ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረዉም በ1992 ነበር።

የዓለም የአዕምሮ ጤና ፌዴሬሽን ቀኑ እንዲከበር የሐሳብ አመንጪ ሲሆን በስሩም ከ150 በላይ ሃገራትን በአባልነት ይዟል።

Share This News

Comment