Logo
News Photo

የኒውክለር ሀይል ሁለንተናዊ እድገትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል ተባለ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ የጥናታዊ ፅሁፍ መድረክ (Seminar) አዘጋጅቷል፡፡ በመድረኩ የኒውክለር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሀገራዊ ፋይዳ፣ የኮምፒዩተር ስክሪን እና የስልክ ሱስ ተፅዕኖዎች እንዲሁም የእብድ ውሻ ንክሻ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የጤና እክሎችን መቆጣጠር በሚያስችሉ ስልቶች ዙሪያ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ 

በተለይ ከኒውክለር ሃይል ጋር ተያይዞ ሊታወቁ ስለሚገባቸው ጉዳዮች፣ የኒውክለር ሀይል ከልማት፣ ለጤና፣ ግብርና እና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ስለሚኖረው ፋይዳ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ የኒውክለር ፊዚክስ ተመራማሪ እና መምህር የሆኑት ዶ/ር ማስረሻ ፈለቀ በዚሁ መድረክ ላይ እንደተናገሩት በሀገር ደረጃ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቅጠል እንዲሁም በጤና፣ ትምህርት እና የግብና ዘርፎችን ለማዘመን የኒውክለር ሀይል ጠቀሜታው የጎላ ስለመሆኑ አውስተዋል፡፡ 

የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል ጥናታዊ መድረኩን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ‘’የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮችን መሰረት አድርጎ ጥናትን መሰረት ያደረጉ የምሁራን ምልከታዎችን እና እውቀቶችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ማድረጉን ይቀጥላል’’ ብለዋል፡፡ 

Share This News

Comment