ከየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን የመጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርሲቲውን የማህበረሰብ ተኮር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያን ጎበኙ
ከየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን
ባለስልጣን የመጡ ባለሙያዎች
የዩኒቨርሲቲውን ኤፍኤም ሬዲዮ
ጣቢያ የጎበኙ ሲሆን
ጣቢያው በአዲስ መልክ
ስራ ከጀመረ
ጀምሮ እያደረገ ባለው
እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ገንቢ
አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የባለስልጣን መስሪያ
ቤቱ ባለሙያዎች:-
ደረጀ ሽታው፥ የህዝብ
መገናኛ ብዙሀን ምክትል
ዴስክ ሀላፊ፣ አየለ
አለማየሁ፥ የማህበረሰብ እና
የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን
ክትትል ከፍተኛ ባለሞያ፣አምሀ
ተረፈ የሚዲያ ቴክኖሎጂ
ከፍተኛ ባለሞያ እንዲሁም
ቤዛ በቀለ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን
ባለስልጣን የድሬደዋ ቅርንጫፍ
ላይዘን ኦፊሰር ሲሆኑ
ሬዲዮ ጣቢያው እየሰራ
ያለውን ስራ አድንቀው የተለያዩ ሙያዊ
እገዛዎችን ለጣቢያው እንደሚያደርጉ
ገልፀዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ
ዋና ስራ
አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር ኤርሚያስ ሙላቱ በበኩላቸው
ጣቢያው ያለውን አቅም
ተጠቅሞ ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ
ኘሮግራሞችን እየሰራ መሆኑን
ጠቁመው በቅጣይ የተለያዩ
አዝናኝ እና አስተማሪ ፕሮግራሞችን በማድረስ
ሰፊ ስራ
እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ
ተኮር ኤፍ ኤም ሬዲዮ 104.5 የተለያዩ
አዝናኝ እና ቁም ነገር አዘል
የሬዲዮ ፕሮግራሞችን እያስተላለፈ
ሲሆን በድሬዳዋ እና
አካባቢው የሚገኝ ማህበረሰብ
ከጣቢያው የሚተላለፉ ዝግጅቶችን
እንዲከታተሉም ጥሪ ቀርቧል፡፡
Share This News