Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለኡጋዝ ሐሰን ሂርሲ መታሰቢያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ርት ቤት ድጋፍ ማድረግ የሚያስችለውን ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በከተማ እና ገጠር አካባበቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ፕሮጀክቶችን ነድፎ እየሰራ ሲሆን የዚሁ ድጋፍ አካል የሆነ እና የኡጋዝ ሐሰን ሂርሲ መታሰቢያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ርት ቤትን መደገፍ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል፡፡ 

ፕሮጀክቱ ለትምህርት ቤቱ መምህራን የ አቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ ዘመናዊ የመማሪያ ግብዓቶች እና ቴክኖሎጂዎችን በድጋፍ መልክ ማቅረብ፣ የትምህርት ቤቱን መሰረተ ልማቶች የማሻሻል እና የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎችን ያካተተ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በፕሮጀክት ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኘተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ወንዲፍራው ደጀኔ እንዳስታወቁት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ማህበርሰብ አቀፍ የልማት ስራዎችን ዩኒቨርሲተው እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን ጥራት ያለው ትምህርትን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ዩኒቨርሲቲው ከመንግስት እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Share This News

Comment