የመጀመሪያው ሩብ አመት የስራ ክንውን ሪፓርት ለዩኒቨርሲቲው መማክርት (Council) ቀርቦ ውይይት ተደረገበት
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎች ለዩኒቨርሲቲው መማክርት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በዛሬው እለት ሁሉም ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤቶች ባለፉት ሶስት ወራት የሰሯቸውን ስራዎች ያቀረቡ ሲሆን ሪፓርቶቻቸውን ተከትሎ ከዩኒቨርሲቲው መማክርት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ''በተቋም ደረጃ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ቢሆኑም የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ ለማሳካት እንዲሁም ሁለንተናዊ ለውጦችን በተቋም ደረጃ ለማምጣት ከዚህ በላይ ልንሰራቸው የሚገቡ በርካታ ስራዎች አሉ'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ለውጥ በጥቂት አመራሮች ጥረት እና ፍላጎት ብቻ አይመጣም ያሉት ፕሬዝደንት ዶ/ር ኡባህ ሁሉንም የዩኒቨርሲቲውን ሰራተኛ በማሳተፍ እንዲሁም ስራ እና ተጠያቂነትን ለሁሉም ሰራተኛ በማጋራት ልንሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በእለቱ ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ በተዋረድ ሁሉም ሰራተኛ እቅድ የሚያዘጋጅበት እንዲሁም ሪፓርት የሚያቀርብበት መተግበሪያ ሶፍትዌር ቀርቦ ምክረ ሃሳብ ተሰጥቶበታል፡፡
Share This News