Logo
News Photo

20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች አና ህዝቦች በዓል በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ተከብሮ ውሏል፡፡ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝደንት ተወካይ የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ‘’ ዩኒቨርሲቲዎች  ትንሿ ኢትዮጵያ ብዝኃ ባህል፣ ብዝኃ ማንነትና ብዝኃ አመለካከት የሚያንጸባርቁ ህብረ-ብሔራዊ ተቋማት በመሆናቸው የጋራ መግባባትን ለመፍጠርና ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የጎላ ድርሻ አለቸው’’ ብለዋል::

የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን በበኩላቸው ‘’ሀገራችን ኢትዮጲያ ለብዝሃነትን እውቅና ሰጥታ እና ብዝሃነትን ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ በመጠቀም የህዝቦችን የዘመናት የእኩልነት ጥያቄ መፍታት ችላለች’’ ብለዋል፡፡

በእለቱ የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ መምህራን የሆኑት መ/ር ናኒ ደበሌ ‘’ፌዴራላዊ ሥርዐት እና ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ’’ በሚል ርዕስ እንዲሁም ረዳት ፕሮፌሰር ኬና ከበደ ‘’ፌዴራል ዴሞክራሲ ግንባታ ተስፋዎች እና ተግዳሮቶች’’ በተሰኙ ርእሶች ዙሪያ ሰፊ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል

የእለቱን መርሃ ግብር አስመልክቶ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል ‘’የወል ትርክቶችን በማጠናከር በመግባባት ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን መገንባት ለሀገር እድገት እና ብልጽግና የማይተካ ሚና አለው’’

Share This News

Comment