Logo
News Photo

22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ኩነቶች ተከብሮ ውሏል

ሙስና በሀገር ብሔራዊ ጥቅም እንዲሁም የህዝቦች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጥቅሞች ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ታሳቢ በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፀረ ሙስና ቀን ይከበራል፡፡ ኢትዮጲያም የሙስናን ፈርጀ ብዙ አደጋዎች እና የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ይህንኑ ወንጀል መከላከል የሚያስችል በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ስትገኝ የፀረ ሙስና ቀን በሀገር ደረጃ በተለያዩ ኩነቶች ታስቦ እንዲውል እና የፀረ ሙስና ተግሉ ሀገራዊ ንቅናቄ እንዲሆን እየሰራች ነው፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሙስናን ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች በመገንዘብ የፀረ ሙስና ቀንን በተቋም ደረጃ የተለያዩ ኩነቶችን በማሰናዳት አክብሯል፡፡ የፀረ-ሙስና ቀን በተቋም ደረጃ በተከበረበት ወቅት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት / ኡባህ አደም እንደተነገሩት ‘’የሙስና ወንጀል በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ በሀገር እንዲሁም በተቋማት ደረጃ መጠነ ሰፊ ጉዳትን እያስከተለ ሲሆን ወንጀሉን ውስብስብነት ታሳቢ ያደረጉ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ልንከላከለው ይገባል’’ ብለዋል፡፡

ሙስና ውስብስብ የወንጀለኞች ትስስር ያለው በመሆኑ የፀረ ሙስና ትግሉ የዜጎችን ሁለንተናዊ ርብርብ እንዲሁም ተቋማዊ የአሰራር ሂደቶችን የማሻሻል ሰፊ ጥረቶችን ይፈልጋል ያሉት / ኡባህ አክለውም ‘’የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሙስናን ከመዋጋት አንፃር አገልግሎቶችን የማዘመን፣ ለዜጎች ቅሬታ አፋጣኝ መፍትሔ የመስጠት እንዲሁም ሙሰኞች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማስቻል መጠነ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል’’ ብለዋል፡፡

ሙሰኞችን ተከታትሎ በህግ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ከሚሰራው ስራ በተጓዳኝ ሙስናን የመከላከል እና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን የማዘመን ስራ ላይ ተቋማት ትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ነው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት / ኡባህ አደም አጥፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት፡፡

በእለቱ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ንብረታቸውን ያስመዘገቡበትን ሰነድ ለዩኒቨርሲቲው ስነ ምግባር መከታተያ ስራ አስፈጻሚ ተውካይ ለሆኑት / ራሄል ለማ አስረክበዋል፡፡ በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው መማክርት (ካውንስል አባላት) ባለ አምስት ነጠብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ሙስና በተቋም ደረጃ በጋራ ለመዋጋት ቃል መግባታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share This News

Comment