Logo
News Photo

በታክስና የጉምሩክ ህጎች ዙሪያ ሲሰለጡ የነበሩ ተማሪዎች ተመረቁ

ድሬደዋ ዩንቨርስቲ ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከጉምሩክ ኮሚሽን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር ከህግ እንዲሁም ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጆች ለተውጣጡ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና በማጠናቀቅ አስመረቀ፡፡ ስልጠናው በታክስና ህጎች እና ጉምሩክ ዙሪያ 2017 ጀምሮ ሲሰጥ መቆየቱ ታውቋል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የገቢዎች ስራ አስኪያጅ አቶ አትሐም መሐመድ እንደተናገሩት ''ሀገራችን ኢትዮጵያ ከዜጎቿ ብዙ ነገር ትፈልጋለች'' ካሉ በኋላ የታክስ አስፈላጊነትን ለሀገራችን ያለውን ጥቅም ማወቅ ከሁላችንም የሚጠበቅ ሃገራዊ ግዴታ መሆኑን አስረድተዋል::

አክለውም "የሀገራችንን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ የታክስ ህጎችን የሚያውቅና የሚተገብር ዜጋን ማፍራት ይኖርብናል’’ ብለዋል::

የጉምሩክ ኮሚሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አብዱልባሲጥ ዑመር ድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ስልጠናው በተሳካ ሁኔታ እንዲሰጥ ላደረገው ከፍተኛ አስተዋፅኦ አመስግነው ወደ ፊት ከዚህ በተሻለ እና በተደራጀ መልኩ ሌሎች አካባቢዎችንም ባካተተ መልኩ ስልጠናውን እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡ አቶ አብዱልባሲጥ ዑመር አክለውም የስልጠናውን የምዘና ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ዳጎስ ያለ ሽልማት እንደተዘጋጀ እና የቅጥርም ሁኔታ እንደሚመቻች አሳውቀዋል::

የድሬደዋ ዩንቨርስቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝደንት ልዩ አማካሪ የሆኑት / በረከት ተስፋዬ ለሁለቱም ተቋማት ምስጋናቸውን አቅርበው ስልጠናው ተማሪዎች በታክስ እና ጉምሩክ ጉዳዮች ሰፊ እውቀት እና ክህሎት ከማስጨጥ ባለፈ ከታክስ አሰባሰብ ሂደቶች ጋር ተያይዞ ለሚስተዋሉ ክፍተቶችን ከማሻሻል አንፃርም ትልቅ ሀገራዊ ጥቅም እንዳለው አስገንዝበዋል::

 

 

 

 

Share This News

Comment