Logo
News Photo

የዓለም የምህንድሳ ቀን "ምህንድስና ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እየተከበረ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ደርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም አቀፍ ደረጃ  የምህንድስና ቀን ሁሌም የካቲት 25 ቀን እንዲከበር ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት  የዘንድሮው የምህንድስና ቀንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ በሃገር አቀፍ ደረጃም ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ "ምህንድስና ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል  እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዛሬው እለትም በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ሲሆን ቀኑን በማስመልከት በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተዘጋጀው ወርክሾፕ ላይ  በምህንድስናው ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድና እውቅና ያላቸው ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፋቸውን አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

Share This News

Comment