ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለፍትሕ ሚኒስቴርና ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያለማውን ሲስተም ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሔደ
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለተቋማቱ ያለማውን በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ፤የወጣት ጥፋተኞች መረጃና የወሲባዊ ጥቃት አድራሾች መረጃ መመዝገቢያ ስርዓት ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ታህሳስ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
የተሰራው ሲስተም በኢትዮጲያ የአስገድዶ መድፈር እና በህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃትን አስመልክቶ ትክክለኛ አሀዛዊ መረጃ ለማግኘት ወሳኝ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በመረጃ እጥረት ምክንያት የፍትህ መጓደልን ከመቅረፍ አኳያ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው በመድረኩ ተገልጿዋል፡፡
በተጨማሪም ሲስተሙ በተደጋጋሚ ወንጀል የሚፈፅሙ፣ በአመክሮ የሚፈቱና ታርመው የሚወጡ ወንጀለኞች ተመልሰው ወንጀል ቢሰሩ የወንጀል ሪከርዳቸው የማይታወቅበት ሂደትን የሚያሻሽል ሲሆን ትክከለኛና አስተማሪ የሆነ ቅጣት ከማሰጠት አኳያ ዐቃቤ ሕግም ሆነ ፖሊስ ደጋጋሚ ወንጀለኛ ነው ብሎ መረጃ ለማቅረብ እንዳይቸገሩ የሚረዳ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
በዕለቱ ሲስተሙን በማበልፀግ ሂደት የነበሩ ሁኔታዎች እንዲሁም ሲስተሙን መጠቀም በሚቻልበት ቴክኒካዊ ክህሎቶች ዙሪያ ሲስተሙን ያበለፀጉት የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ መሰል ማብራሪያዎች እና ስልጠናዎች በቀጣይ ለሚመለከታቸው አካላት ተከታታይነት ባለው መልኩ እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡
በመድረኩ የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ተማም አወልን ጨምሮ፣ የፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ሃላፊዎች እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተወከሉ ባለድረሻ
Share This News