Logo
News Photo

የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች መድረክ በ አሶሳ እየተደረገ ነው፡፡ ዶ/ር ኡባህ አደም የጥምረቱ ፕሬዝዳንት እና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መድረኩን በይፋ ከፍተዋል፡፡

3ኛው የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲዎች መድረክ (Consortium of Applied Sciences ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ርዕሰ መዲና አሶሳ ከተማ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ መድረኩ የ15 ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና ተመራማሪዎችን ያሳተፈ ሲሆን በኢትዮጲያ ተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎችን በሚመለከት በርካታ ውይይቶች እና ውሳኔዎች እንደሚተላለፉበት ይጠበቃል፡፡

የጥምረቱ ሰብሳቢ እና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት  ባደረጉት ንግግር ‘’የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች እስካሁን በሰሯቸው የለውጥ ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት የሚያደርጉበት፣ ልምድ እና ተመኩሮ የሚለዋወጡበት እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎቹ ትብብር የተሰሩ ፕሮጀክቶችን ውጤት በመመልከት መሰል ሀገር አቀፍ ትብብሮችን የሚያጠናክሩበት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

የጥምረቱ ፕሬዝዳንት አክለውም ’በአሶሳ እና አካባቢው ባየነው ፀጋዎች ተደመናል ያሉ ሲሆን ’’በየአካቢቢዎቻችን የሚገኙ ፀጋዎቻችንን መነሻ በማድረግ የሚሰሩ የተግበር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የዛሬው መድረክ በተለመደው መልኩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበውበት ብቻ የሚጠናቀቅ አይሆንም ያሉት ዶ/ር ኡባህ ’’በሚቀርቡ አጀንዳዎች መነሻነት ሰፊ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን (Resolutions) በማስተላለፍ ለቀጣይ ስራዎች የምንዘጋጅበት ይሆናል’’ 

መድረኩ በዚህ ሰዓት የቀጠለ ሲሆን ነዋሪነታቸውን በካናዳ ያደረጉት ፕሮፌሰር አብዲ ኢድሪስ ያካበቱትን ልምድ እና እውቀት አንዲሁም ነባራዊ ተሞክሮ (Practical Experience) ለዩኒቨርሲቲ አመራሮች እያካፈሉ ይገኛል፡፡

Share This News

Comment