Logo
News Photo

በ3ኛው የተግባር ሳይንስ ጉባኤ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መልካም ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት ተደረገባቸው

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ወደ ተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርገው የሽግግር ስራ አካል የሆነው ዓለም አቀፍ ፕሮጀክቶችን የመስራት ተመኩሮ በጉባኤው ላይ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ 

The Ethiopia-Djibouti Females at Makerspace እና Methodology and Didactic Education for University of Applied Science የተሰኙ ሁለት ዓለም አቀፍ ምርምሮች እና ምርምሮቹን ለመስራት የተግባር ሳይንስ ዩኒርሲቲዎች ትብብር ሚናን በተመለከተ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የምርምር ፕሮጀክቶቹ አስተባባሪ የሆኑት መ/ርት ሃና ጌታቸው አቅርበዋል፡፡ 

መ/ርት ሃና በሁለቱ ፕሮጀክቶች የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ና ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም አቀፍ ፕሮጀክቶቹን ለማሸነፍ ስለነበራቸው ጥረቶች፣ ያሸነፏቸውን ፕሮጀክቶች ባህሪያት እና በፕሮጀክቶቹ ትግበራ ስለተገኙ ውጤቶች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ዓለም አቀፍ ፕሮጀክቶችን ተወዳድሮ ለማሸነፍ የዩኒቨርሲቲዎች ትብብር ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት መ/ርት ሃና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን ከሌሎች የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

3ኛው የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች መድረክ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት እና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ቀጣዩን መድረክ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅ እንዲሆን ተመርጧል፡፡

Share This News

Comment