Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራኑ የገነባቸው የመኖሪያ ቤቶችን አስመረቀ NBC Ethiopia

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመምህራኑን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ያለመ የመምህራን የመኖሪያ ቤቶችንና እየተጠናቀቀ የሚገኘውን ሪፈራል ሆስፒታል ስራዎችን ጨምሮ ሰባት ፕሮጀክቶችን አስመረቀ።

የፕላንና ልማት ሚኒስትርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ፍፁም አስፋው ዩኒቨርሲቲው ለመምህራን የመኖሪያ ቤቶችን መገንባቱ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት በቀጣዮቹ አምስት አመታት 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት ከተያዘው ቁርጠኝነት የሚጣጣም መሆኑን ተናግረዋል።

መምህራን ለትምህርት ጥራትና ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማይተካ ሚና አላቸው ያሉት ሚኒስትሯ፤ የዩኒቨርሲቲው ተግባር ለመምህራን የኑሮ መሻሻል ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት መሆኑን ጠቁመዋል።

ዩኒቨርሲቲው ገፅታውን ለመገንባትና የዩኒቨርሲቲውን ብሎም የአካባቢውን ማህበረሰብ እርካታ ለመጨመር ቁርጠኝነቱን በሌሎቹ ባስመረቃቸው ፕሮጀክቶችም ማሳየቱን ጠቁመዋል።

የዩኒቨትሲቲው ፕሬዝዳንት ኡባህ አደም (/) የተመረቁት ፕሮጀክቶች የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና የአካባቢው ማህበረሰብን እርካታ ለመጨመር የተከናወኑ መሆናቸውን ተናገረዋል።

ፕሬዝዳንቷ ዩኒቨርሲቲው የመምህራንን ፍልሰት ለመቀነስ ያለመ የመምህራንን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የመኖሪያ ቤቶቹ መገንባታቸውን ገልፀዋል።

የመኖሪያ ህንፃዎቹ 267 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ከመሆናቸው ባሻገር የህፃናት ማቆያን ያካተቱ እንደሆኑም ጠቁመዋል።

በመጠናቀቅ ላይ ያለው የዩኒቨርሲቲው ሪፈራል ሆስፒታል በሙሉ አቅሙ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ለማድረግ የኤለክትሮመካኒካል ስራዎች እንደተሰሩለትም ገልፀዋል።

ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከልም ለዩኒቨርሲቲው የውሃ ማጣሪያና ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃን ጨምሮ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ የሚያግዙ ፕሮጀክቶች እንደተሰሩለት ተናግረዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ዩኒቨርሲቲው ለመምህራን የመኖሪያ ህንፃን መገንባቱ የከተማዋን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል የሚረዳ ነው ብለዋል።

Share This News

Comment