Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 7 ታላላቅ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲውን ገፅታ የሚቀይሩ፣ ምቹ የስራ አካባቢን የሚፈጥሩ፣ የፀጥታ እና ደህንነት ስራዎችን በእጅጉ የሚያግዙ፣ ለተማሪ የሚሰጥ አገልግሎትን የሚያሻሽሉ፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግሮች የሚቀርፉ እንዲሁም ዘመናዊ የህክምና አገልግሎትን መስጠት የሚያስችሉ ስራዎችን በብዛት አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡ 

በፕሮጀክት ማስመረቂያ መርሃ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር፣ ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር እና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራረ ቦርድ ሰብሳቢ፣ ክቡር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት፣ ስራ ስምሪት እና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ክብርት ዶ/ር ኡባህ አደም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር መስፍን ነገዎ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ የፌደራል መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተገኝተው መርቀዋል፡፡

Share This News

Comment