Logo
News Photo

“የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራር ዩኒቨርሲቲው የገጠመውን የሰላም እጦት በመቅረፍ የተረጋጋ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን አስችሏል እንዲሁም በርካታ የመሰረተ ልማት ትሩፋቶችን ማስዝገብ ጀምሯል”

ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 7 ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ባስመረቀበት መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ዩኒቨርሲቲው ከቅርብ አመታት ወዲህ እየከወነ ያለውን የመሰረተ ልማት ስራዎች፣ የመማር ማስተማር ሂደትን የማዘመን እንቅስቃሴ፣ የተቋማትን አሰራር የሚያዘምኑ ቴክኖሎጂዎችን የማበልፀግ ተሞክሮ እንዲሁም በምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎቶች ስራዎች እየታየ ያለው እምርታ የዩኒቨርርሲቲውን አመራር የሚያስመሰግን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተለይ የመምህራን መኖሪያ መንደርን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም የነበራቸውን ከፍተኛ ጥረት እና ቁርጠኛ አመራር ያደነቁት ክብርት ሚኒስቴሯ ስራው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ጥብቅ ክትትል ድጋፍ በማድረግ፣ ችግሮች ሲገጥሙ አፋጣኝ መፍትሔዎችን በማፈላለግ ያለመታከት ሰርተዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

ፕሮጀክቶችን ጀምሮ ለመጨረስ በርካታ ተግዳሮቶችን ማለፍ ይጠይቃል ያሉት ዶ/ር ፍፁም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት ችግሮችን ተቋቁሞ መፍትሔ በመጠቆም እና ተደጋግፎ ተቋሙን በመምራት ትልቅ ስራ መስራት ተችሏል ብለዋል፡፡

Share This News

Comment