ዩኒቨርሲቲው ትምህርት ክፍሎችን ከ ኢንዱስትሪዎች ጋር ለማስተሳሰር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ
የጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል ለተመራቂ ተማሪዎች የሽኝት እንዲሁም ትምህርት ክፍሉን ለተቀላቀሉ አዲስ ተማሪዎች የ"እንኳን ደህና መጣችሁ" አቀባበል መርሃ-ግብር አካሂዷል።
በዕለቱ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር በረከት ተስፋዬ፤ የትምህርት ክፍሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ ያላቸውን ቅርርብና ተግባቦት በማሳደግ ረገድ እያከናወነ ያለውን ስራ አድንቀዋል። የጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል በ one week class for industry expert መርሃ ግብር እያደረገ ያለውን ተሳትፎ ያስታወሱት ዶ/ር በረከት ተማሪዎች ወደፊት ከሚሰሩበት ተቋም/ኢንዱስትሪዎች ጋር ተቀራርቦ የመስራት፣ ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጉትን እውቀት እና ክህሎት የማግኘት እድል እንዲያገኙ ከማስቻል አንፃር ት/ርት ክፍሉ ለሚያደርገውን ጥረት ምስጋና አቅርበዋል::
የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን አቶ ሰብስቤ ጌታሁን በበኩላቸው ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የሚቀስሙትን የንድፈ-ሀሳብ ትምህርት በግቢው ውስጥና ከግቢ ውጭ ባሉ ሚዲያዎች ላይ በተግባር እየቀየሩት እንደሚገኙ ገልፀዋል።
የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ረ/ፕሮፌሰር እዮብ ነጋ የመርሃ-ግብሩን ዓላማ ሲያብራሩ፤ ተመራቂዎችን በክብር ለመሸኘት፣ አዲስ ገቢዎችን ለመቀበልና ተማሪዎች በቆይታቸው እንዲተጋገዙ ለማስቻል መሆኑን ገልፀዋል። አክለውም ትምህርት ክፍሉ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆነውም በዕውቀትና በስነ-ምግባር የታነፁ ጋዜጠኞችን ለሀገሪቱና ለአስተዳደሩ ሚዲያዎች እያበረከተ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም ተማሪዎችን ከአስተዳደሩ የሚዲያና ኮምኒኬሽን ተቋማት ጋር የማስተሳሰር ስራ በስፋት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
Share This News