ፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ፣ ዘመናዊ የልብስ ስፌት እና ፋሽን ዲዛይን መስሪያ ማእከላት (Workshop) በዛሬው እለት ተመርቀዋል
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎኪ ኢንስቲትዩት የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ እንዲሁም ዘመናዊ ልብሶች የሚሰፉበት እና የዲዛይን ስራ የሚሰራበት መስሪያ ማእከላትን በማደራጀት ዛሬ አስመርቋል፡፡ ማእከላቱ ለዩኒቨርሲቲው፣ ለተለያዩ የጤና ተቋማት፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ኢኑዱስትሪዎች እና ድርጅቶች የሚያገለግሉ የልብስ፣ የገላ እና የእቃ ማጠቢያ ሳሙናዎች እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ አልባሳትን ማምረት የሚችሉ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ማእከላቱን መርቀው የከፈቱት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ዩኒቨርሲቲው የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ መጠን ተቋሙ ያለውን የሰው እና የመሳሪያ አቅም በመጠቀም ለተማሪዎች በተግባር የተደገፈ ትምህርት በመስጠት፣ ቴክኖሎጂዎችን በማበልፀግ እና በማሸጋገር እንዲሁም የማህበረሰቡን ችግር የሚቀርፉ ምርቶችን በማምረት ግንባር ቀደም ሚና ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
የቴክኖሎጂ ኢንቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ቤካ በበኩላቸው ማእከላቱ በኢንስቲትዩቱ መምህራን በዉስጥ አቅም መደራጀታቸውን አስታውሰው ማዕከላቱ ለማህበረሰቡ ሊቀርቡ የሚችሉ ምርቶችን በማምረት ለዩኒቨርሲው ገቢ ማመንጨት የሚችሉ ናቸው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ግርማ አክለውም ዛሬ ከተደራጁት ማዕከላት በተጨማሪ የዉስጠ ገቢ ማመንጨት የሚችሉትን ተጨማር ማዕከላትን የሰዉ ሃይል ለማደራጀት ጥናት እየተሰራ መሆኑንጠቁመዋል፡፡
Share This News