Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት አባላት ታህሣስ 26 ቀን 2018 ዓ/ም አረጋዊያንን ለመደገፍ ታስቦ በሚካሄደው የሩጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

ዳዊት አረጋዊያን መርጃ ማዕከል ባዘጋጀው በዚሁ የሩጫ ውድድር ላይ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የመሮጫ ቲሸርቱን በመግዛት ከወዲሁ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ 

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በበጎ ስራ ላይ የተሰማሩ በርካታ ድርጅቶችን በመደገፍ ሰፊ ስራ እየሰራ ሲሆን ታህሳስ 26 በሚካሄደው የሩጫ ውድድር ላይም ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲውን አመራር ጨምሮ፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ተማሪዎችን በማስተባበር ተሳትፎ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ 

#እኛም_አረጋዊያንን_ለመደገፍ_እንሮጣለን!!

Share This News

Comment