የቃል ኪዳን ቤተሰብ ምስረታ መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ፡፡
አንደኛ አመት ተማሪዎችን ከድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ቤተሰባዊ ትስስር እንዲፈጥሩ የሚያስችል የቃል ኪዳን ቤተሰብ የተሰኘ መርሃ ግብር ባዛሬው እለት በደማቅ ስነ ስርዓት ታጅቦ ተካሂዷል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት “ሀገራችን ኢትዮጲያ በዘመናት ሂደት ውስጥ በርካታ የጋራ እሴትን ያፈሩ ህዝቦች መኖሪያ፣ በደጉ ጊዜ እርስ በእርስ የተጋባን፣ በንግድ እና ታሪክ የተሳሰርን፣ ወግ እና ባህል የተዋረስን፣ በበርካታ ማህበራዊ እሴቶች ተሳስረን አብረን ለዘመናት የዘለቅን ፣ በክፉ ጊዜያት ደግሞ ጠላትን በጋራ የመከትን፣ ያለንን ተካፍለን የበላን ድንቅ ህዝቦች ነን’’ ብለዋል፡፡
ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ የህብረ ብሔራዊነት መገለጫ እና የከተማዋ ሁነኛ ሃብት ነው ያሉት ዶ/ር ኡባህ አክለውም “ዩኒቨርሲቲው ሀገራዊ እሴቶቻችን ተጠብቀው እንዲቆዩ ሰፊ ስራዎቸን የሚሰራ፣ ከህዝብ እና መንግስት የተሰጠውን ሀላፊነት ለመወጣት የሚታትር እና በከፍተኛ ተቋማዊ የለውጥ ሂደት ውስጥ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ነው’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው ‘’የቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት ፍቅርና አብሮነትን ለማጠናከር ከፍተኛ የሆነ ድርሻ ይኖረዋል ያሉ ሲሆን ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ከማጠናከር አንፃርም አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቁመዋል። ምክትል ከንቲባ ክቡር ሃርቢ አያይዘውም አስተዳደሩ ይህን ፕሮጀክት ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን በማረጋገጥ የቃል ኪዳን ቤተሰቦች የድሬዳዋን ገፅታ ከማስተዋወቅ አንጻር የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Share This News