የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል የ6 ወር ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለሆስፒታሉ ቦርድ አቀረበ
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል ስራ አመራር ቦርድ የሆስፒታሉን የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ሰምቶ ቀጣይ የስራ መመሪያ ሰጥቷል፡፡ ቦርዱ በተጨማሪም ሆስፒታሉ ያዘጋጀውን የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ እንዲሁም የአጋርነት እና ትብብር ስራዎች እቅድ ሰምቶ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታሉ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም በምክትል ከንቲባ ማእረግ የመንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በዚሁ መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሆስፒታሉ በሂደት መሻሻሎችን እያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል ከአካባቢው ማህበረሰብ አልፎ ለአጎራባች ክልሎች እና ሀገራት ጭምር አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተገነባ መሆኑን ያስረዱት ክቡር አቶ ኢብራሂም የሆስፒታሉን ርዕይ ለማሳካት ብሎም ሀገራዊ ትልሞችን እውን ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ተሰጠቶ ሊሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሁሴን መሀመድ የሆስፒታሉን የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ዶ/ር ሁሴን በሪፓርታቸው ሆስፒታሉ በስድስት ወራት ውስጥ የከወናቸውን አበይት ተግባራት እና ውጤት አመላካቾች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በተለይ ተጨማሪ የህክምና አገልግሎቶችን ከመስጠት፣ ሆስፒታሉን በሰው እና በቁሳቁስ ግብዓቶች ከማደራጀት እንዲሁም ጥራት ያለው አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር የተሰሩ ስራዎችን ለቦርዱ አቅርበዋል፡፡
Share This News