Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው የመጀመሪያው የብዝኃነት ፎረም "ብዝኃነታችን ለብልጽግናችን" በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ይገኛል፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ "ብዝኃነታችን ለብልጽግናችን" በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያውን የብዝኃነት ፎረም  በዛሬው እለት በቢፍቱ ሞል የመሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ሲሆን በፎረሙ ላይ በመገኘት የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት የተከበሩ አቶ ሀርቢ ቡህ እንደተናገሩት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር ከሚያከናውነው ሀገራዊ ተልዕኮው ጎን ለጎን እንደ ሀገር ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸውን የጋራ የምክከር መድረኮችን በማሰናዳት ትልቅ ኃላፊነት እየተወጣ የሚገኝ የከፍተኛ የትምህርት ተቋም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አቶ ሀርቢ አክለውም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ድሬደዋ ከቅርብ ዓመት ወዲህ ልዩነትን ባልተገባ መንገድ በመጠቀም በህዝቦች መካከል ግጭቶች እንዲቀሰቀሱ በማድረግ በህዝቦች መካከል ለዘመናት የዘለቀውን  ጠንካራ ትስስርን ለማላላት የሞከሩ እኩይ ተግባራት ተፈፅመዋል፡፡ የዚህ አይነቱ ከፋፋይና እጥፊ የሆነ እኩይ ድርጊት ዳግም ተመልሶ የህዝባች ስጋትና የልማታችን ማነቆ እንዳይሆን በግልፅ የመወያየት ባህላችንን በማዳበር በሀገራችን ሰለምና ደህንነት በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ቤተ እምነቶች፣ የትምህርት ተቋማት እና የሚዲያ አካላት የሚኖራቸው ሚና የጎላ በመሆኑ  ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳነት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸው ሀገራችን የበርካታ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ ከመሆኗም ባሻገር የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባት እና የተለያዩ ሀይማኖትች የሚገኙባት ሀገር እንደመሆኗ ብዝኃነት ማስተናገድ  ይኖርባታል ብለዋል።

ዶ/ር ኡባህ አክለው ከ70 በላይ ብሔር ፣ ብሔረሰብና ህዝቦች የሚኖሩባት የትንሻ ኢትዮጵያ ተምሳሌት ተብላ የምትጠራው ድሬደዋም ያላትን ተከባብሮ በሰላምና በፍቅር አብሮ የመኖር እሴቷን በአግባቡ መጠቀም እንዲቻልና ለተቀረው የሀገራችን ክፍልም ለማስተዋወቅ የዚህ አይነት መድረኮች መዘጋጀታቸው ያላቸው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከሚሰራቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንዱ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በመሆኑ የድሬደዋ ከተማ ከብዝኃነት አንፃር ያሏትን ፀጋዎች ተጠቅመን ለዲሞክራሲ ግንባታ፣  ለህዝቦች እኩልነት ፣ ለፍትሀዊ ተጠቃሚነት መዋል እንዲቻል ታስቦ ፎረሙ መዘጋጀቱን የገለፁት ዶ/ር ኡባህ እንደዚህ አይነት መድረኮች ቀጣይነት ይኖረዋል ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን በበኩላቸው በብዝኃነት ፎረሙ መድረክ እስካሁን ያለፈበትን ሂደትና በቀጣይ ሚኖረውን ገፅታ የሚያሳይ ጥናት አቅርበዋል፡፡

በፎረሙ ላይ ተዋቂው ምሁር፣ ደራሲ ገጣሚ እና ተመራማሪ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ የመድረኩን ቁልፍ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ብዝኃነትን የሚያስተናግድ ትውልድ ለመፍጠር ከእንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ መሰራት ይኖርበታል ለዚህ  ስኬትም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

በፎረሙ ላይ ተገኝተው ብዝኃነት በኢትዮጵያ ትናት፣ ዛሬ እና ነገ በሚለ ዶ/ር ንጉሱ አክሊሉ ጥናታዊ ጽሁፋቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።


Share This News

Comment