Logo
News Photo

ሀገር አቀፉ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial) ፈተና መሰጠት ተጀመረ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ወስደው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የሚቀላቀሉ ተማሪዎችን ሀገር አቀፍ ፈተና ማስፈተን ጀምሯል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዛሬ መሰጠት የጀመረውን ፈተና ቁጥራቸው 937 የሚሆኑ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መፈተን መጀመራቸው ታውቋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፈተናው በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ እንዲሁም የፈተና ስነ-ምግባር እና ደንብ ተጠብቆ እንዲሰጥ ሰፊ ዝግጅት ያደረገ ሲሆን ተፈታኞችንም ለፈተና የማዘጋጀት እና የፈተና መስጫ የኮምፒተር ላብራቶሪዎችን በማዘጋጀት ሰፊ የዝግጅት ስራ በመስራት ፈተናውን ዛሬ አስጀምሯል፡፡

ፈተናው እስከ ፊታችን ሰኔ 3 ቀን 2018ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣው የፈተና መርሃ ግብር ያስረዳል፡፡

Share This News

Comment