Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው የቴክኖሎጂ ሽግግር የፖሮፖዛል ግምገማ መድረክ ተካሄደ፡፡

የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትብብር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር  ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው የፕሮፖዛል ግምገማ ላይ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘጅዝዳንትና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን እንደገለፁት የቴክኖሎጂ ሽግግርን አስመልክቶ የሚደረጉ የጥናትና የምርምር ስራዎች የማህበረሰቡን ህይወት በሚቀየር መልኩ መዘጋጀት እንደሚኖርበት ገልጸዋል።

በተለይም የአካባቢያችን ማህበረሰብ ከድህነት ተላቆ የተሻለ ህይወትን መምራት እንዲችል አዳዲስና የተሻሻሉ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ምርምሮች መደረግ አለባቸው ያሉት ዶ/ር ሰለሞን የቴክኖሎጂ ሽግግርን አስመልክቶ ለሚደረጉ የጥናትና የምርምር ስራዎች ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ድጋፍና እገዛ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ወንዲፍራው ደጀኔ የቴክኖሎጂ ሽግግግርን አስመልክተው የሚደረጉት የጥናትና የምርምር ስራዎች የአካባቢውን ማህበረሰብ ትክክለኛ ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገቡ መሆን እንዳለባቸው ገልጸው በዚህ ረገድም ተመራማሪዎች በአካባቢያቸው የሚኖረው ማህበረሰብ ችግርን በጥልቀት በመመርመር የተሟላ መረጃ ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ለአንድ ቀን በቆየውና የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረቱን ባደረገው የፕሮፖዛል ግምገማ መድረክ ላይ ስድስት  ፕሮፖዛሎች ቀርበው በመምህራን እና በተመራማሪዎች  ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡  


Share This News

Comment