Logo
News Photo

ለድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ለቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህራን (Intergovernmetal Fiscal Transefer ) አስመልክቶ ስልጠና ተሰጠ።

ለሦስት ቀን የቆየውን ስልጠና በንግግር የከፈቱት በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንትና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን እንዳሉት ኮሌጁ በራሱ ተነሳሽነት ለቀጣይ የተቋሙ አድገት ትልቅ ጥቅም ሊሰጥ የሚችለውን የዚህን አይነት ስልጠና ማዘጋጀቱን አድንቀው ይኽው ተግባር በሌሎችም ኮሌጆች ሊተገበር የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በስልጠናው ከንድፈ ሃሳብ አልፎ አንድን ስራ በተግባር እንዴት መከናወን እንደሚቻል በስፋትና በጥልቀት የሚያሳይ በመሆኑ መምህራን በቂ እውቀት አግኝተው ለተማሪዎቻቸው በማካፈል በገበያ ላይ ተወዳደሪ የሆነ ብቁና የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ያስችላል በማለት ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን ረ/ፕሮፌሰር ነፃነት ሽፈራው በበኩላቸው መምህራን ከንድፈ ሀሳብ ባለፈ ተግባራዊ እውቀት እንዲጨብጡ በተለያዩ ጊዜያት ኮሌጁ ስልጠናዎችን ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር እያዘጋጀ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው የአሁኑ ስልጠናም በተለይ የኮሌጁ መምህራን በክልልና በፌደራል መንግስት መካከል ያለውን የበጀት ድልድልና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከንድፈ ሃሳብ ባለፈ ተግባራዊ  እውቀታቸውን የሚያሳድግ ስልጠና ማግኘታቸውንም ተናግረዋል፡፡ 

ለሦስት ቀን በቆየው ስልጠና ላይ ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህራን በተጨማሪ  ከሀረማያ፣ ከጂጅጋ፣ ከቀብሪዳር እና ከኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመጡ ምሁራን በስልጠናው ላይ ተሳታፊ እንደሆኑበት ለማወቅ ተችሏል፡፡  


Share This News

Comment