Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ህግ ኮሌጅ 3ኛው ዙር የፕሮፖዛል ግምገማ መድረክ አካሄደ፡፡

በግምገማዊ መድረኩ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፋት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገለግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን ምርምርን አስመልክቶ በህግ ኮሌጅ በኩል አሁን ካለው በበለጠ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ያስፈልጋል በማለት አስገንዝበዋል፡፡

በኮሌጁ የምርምር ሰነ-ምግባር ኮሚቴ (Research Ethical Committee) በቅርቡ ተቀርፆ ተግባራዊ ይደረጋል ያሉት ዶ/ር ሰለሞን ለዚሁ ስኬትም የኮሌጁ መምህራንና ተመራማሪዎች የበኩላቸውን ጥረት ያደርጉ ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ለግማሽ ቀን በቆየው የፕሮፖዛል ግምገማዊ መድረክ ላይ የኮሌጁ መምህራን፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ-መብት ካዉንስል ምስራቅ ሪጅን ቅርንጫፍ ተወካዮች፣ የህግ ኮሌጁ የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች እና ከተለያዩ ተቋማት የመጡ ተሳታፊዎች በግምገማዊ መድረኩ ላይ ተካፋይ የሆኑበት ሲሆን በተፈናቃዮች መብት፣ በማህበረሰብ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በመማር ማስተማር የአማርኛ ቋንቋ አጣቀቀም ጋር ተያይዞ ከህግ ረገድ ያሉ ከፍተቶች እና ሊያስከትሉ የሚችሉ የመብት ጥሰቶች አስመልክቶም ሦስት ፕሮፖዛሎች ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡


Share This News

Comment