Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በ23 ሚሊዮን ብር ወጪ ሁለት የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮን ለማከናወን አትላስ ከተሰኝ የውሃ ቁፋሮ ድርጅት ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የውል ስምምነቱን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በኩል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ሲፈርሙ በአትላስ የውሃ ቁፋሮ ድርጅት በኩል ደግሞ ሚ/ር ኦስማን ኑሪ ፈርመዋል፡፡ 

በዚሁ ወቅት የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም እውነቱ እንደገለፁት በዩኒቨርሲቲው ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ የመጣውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ በ23 ሚሊየን 296 ሺህ 7 መቶ ብር ወጪ የሁለት ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ለማከናወን አትላስ ከተሰኘው የውሃ ቁፋሮ ድረጅት ጋር የውል ስምምነት መደረጉን ገልጸዋል።

በውሉ መሠረት ድርጅቱ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ የጉድጓድ ቁፋሮውን አጠናቆ ሁለቱንም ጉድጓዶች ለዩኒቨርሲቲው ያስረክባል ያሉት ዶ/ር አብርሃም በዚህም ዩኒቨርሲቲውን የራሱ የሆነ የውሃ ጉድጓዶች እንዲኖሩት ከማስቻሉም በላይ  ለረጅም ጊዜ በተቋሙ ከፍተኛ ችግር ሆኖ የዘለቀውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር በመቅረፍ በዩኒቨርሲቲው  በውሃ እጦት ምክንያት በተማሪዎች፣ በመማር ማስተማሩ እና በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ላይ ሲፈጥር የነበረውን ጫና በከፍተኛ መጠን ይቀንሰዋል በማለት ተናግረዋል፡፡    

Share This News

Comment