Logo
News Photo

ለድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የቤተ-ሙከራ እና የወርክሾፕ ባለሞያዎች የላብራቶሪ አጠቃቀምና ተያያዥነት ያላቸው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ።

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የቤተ-ሙከራ እና ወርክሾፕ አስተዳደር እና የት/ት ጥራት ዳይሬክቶሬት ባዘጋጁት የሁለት ቀን ስልጠና ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ተልዕኮውን ስኬታማ በማድረግ ብቁና የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት እንፃር  ተማሪዎች ከንድፈ ሃሳብ በዘዘለለ በተግባር የተደገፈ እውቀት ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡ 

ይህን ለማሳካት ደግሞ ዩኒቨርሲቲው ዘመኑ ያፈራቸውና የተሟሉ ቤተ-ሙከራዎች እና ወርክሾፖች ሊኖሩት ይገባል ያሉት ዶ/ር ኡባህ እነዚህ ቤተ-ሙከራዎች እና ወርክሾፖች በሚፈለገው መንገድ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ የሚሰሩ ባለሞያዎችና መምህራን ሰለሚሰሩብት ከፍልና መሣሪያዎቹ  በቂ አውቀት ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ በተዘጋጀው ስልጠና ላይ ተሳታፊ የሆኑ ባለሞያዎች በስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ተጠቅመው የተጣለባቸውን ኃላፊነት ይወጡ ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ ሳይንትፊክ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ገዳፋዬ በበኩላቸው ቤተ-ሙከራዎች እና ወርክሾፖች ውድ በሆነ ዋጋ የተገዙ የተለያዩ መሣሪያዎች የተደራጁ እንደመሆናቸው በእነዚህ ክፍሎች የሚሰሩ ባለሞያዎች እነዚህ መሣሪያዎች ለረጅም ዓመት ማገልገል እንዲችሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡ 

ስልጠናው የባለሞያዎችን አቅም ከማሳደግ ባለፈ ዩኒቨርሲቲው በውድ ዋጋ ከገበያላይ የገዛቸውን  የቤተ-ሙከራ መገልግያ መሣሪያዎች ደህንነት እንዲጠበቅና ሊከሰት የሚችልን አደጋ ከመቀነስ አኳያም ፋይዳው የጎላ ነው በማለት የሳይንትፊክ ዳይሬክተሩ አቶ ቴዎድሮስ አብራርተዋል፡፡

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የቤተ-ሙከራና ወርክሾፕ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ማስረሻ ፈለቀ ለሁለት ቀን በቆየው ስልጠና ላይ በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ቤተሙከራና ወርክሾፕ ውስጥ የሚሰሩ ባለሞያዎች ተሳታፊ የሆኑበት ሲሆን በLaboratory Safty , Laboratory facility ,  Laboratory Material Handling and West disposal, General Requirement for the competence of Testing and calibration Laboratories and general Common Problem in laboratory በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ 

በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች በዩኒቨርሲቲው የኬሚስትሪ ቤተ-ሙከራን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

Share This News

Comment