Logo
News Photo

በድሬደዋ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል ለማቋቋም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግልት ዳይሬክቶሬት በድሬደዋ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል ለማቋቋም ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ለማድረግ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ  የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግልት ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ሱሶች ምክንያት ለስነ-ልቦና ጤና ችግር የሚጋለጡት የህብረተሰቡ ክፍሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው ይህም በማህበራዊና በምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴያችን ላይ አሉታዎ ተፅእኖ እያስከተለ ይገኛል ብለዋል፡፡ 


ዶ/ር ሰለሞን ጨምረውም እንደተናገሩት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው በቅርቡም በድሬደዋ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል እንዲቋቋም  ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 


በውይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ ተቋማትን በመወክል  የተገኙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደ የመጣ መሆኑን ጠቅሰው ይህን መዕከል ለመገንባትም ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፈልጋል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ 


በዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግልት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ወንዲይፍራው ደጀኔ በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ ላይ በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የተሳተፉትን ሁሉንም ተሳታፊዎች አመስግነው በቀጣይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀራርበው በመነጋርና የአጭርና የረጅም ግዜ የድርጊት መርሃ-ግብር በማውጣት ተከታታይ መድረኮችን በማዘጋጀት እና የእቅዳቸው አካል እንዲሆን ዩኒቨርሲቲው እንደሚሰራ ገልፀው ተሳታፊዎችም በየተቋማቸው የሚገኙትን ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች እና የአካባቢያቸውን ማህበረሰብ ስለችግሩ አሳሳቢነት በጥልቀት እንዲረዱት በማድረግ  ሰፊ ንቅናቄ በመፍጠር የበኩላቸውን ይወጡ ዘንድ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡  


Share This News

Comment