Logo
News Photo

በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለሶስተኛው ዙር ሴሚናር በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡

ለሶስተኛው ዙር በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሴሚናር በምርምር ህትመት፣ ዶክሜንቴሽንና ስርጭት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በድሬዳዋ ዮኒቨርሲቲ  ተካሄደ፡፡ 

 

የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም እውነቱ በዚሁ ሴሚናር ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መምህራን ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ጠቁሟል፡፡ አክለውም እንደዚህ ዓይነት ሴሚናሮች በየጊዜው መዘጋጀታቸው በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እንዱሁም ትምህታዊ ወይይትና ክርክር እየተደረገ ያለውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን አሳውቋል፡፡ በተጨማሪም መምህራን ወቅታዊና ሀገራዊ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ የበኩላቸውን ይወጡ ዘንድ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡   

 

የዩኒቨርሲቲው የምርምር ህትመት፣ ዶክመንቴሽንና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር ዶ/ር መሐመድ ቃሶ የምርምር እና ማህበረሰብ አግልግሎት ም/ፕሮዝዳንትን ወክሎ የመዝጊያ ንግግር አድረጓል፡፡ በዚህም ንግግራቸው በ2014 በጀት ዓመት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለሶስተኛ ጊዜ ሴሚናር በተለየዩ ርዕሶች ቀርቦ ወይይት የተከሄደባቸው መሆኑን ጠቁመው በሴሚናሮቹ ላይም በተለያየ ደረጃ የተሳተፉትን ተሳታፊዎች አመስግኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ወደፊት በሉት ተመሳሳይ መርሃ ግብሮች ለይ መምህራን የላቀ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጠይቋል፡፡   

 

በዚህ ሴሚናር ላይ ሶስት ጥናታዊ ጽሁፎች በዩኒቨርሲቲው መምህራን ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በሴሚናሩ ላይ ቁጥራቸው ከሃምሳ (50) በላይ የሚሆኑ መምህራን ተሳትፈውበታል።


Share This News

Comment