Logo
News Photo

በድሬደዋ ዩኒቨርሰቲ ልዩ የሴቶች የምርምር ንድፈ ሀሳብ የግምገማ መድረክ ተካሄደ፡፡

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግልት ም/ፕሬዝዳንት ባመቻቸው የማበረታቻ የጥቅል አገልግልት በዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን የተዘጋጁ 22 የምርምር ንድፈ ሀሳቦችን በመድረክ ላይ ቀርበው ግምገማ ተደርጎባቸዋል፡፡ 

በዚሁ መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በዩኒቨርሲቲው ዝቅተኛ ሆኖ የቆየውን የሴት መምህራን በመርምር ስራዎች ላይ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

በቅርቡም የዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራንን በመርምር ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ስልጠና በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ታወቂ የሀገራችን ምሁራን እንዲያገኙ በማድረግ ሴቶችን የማብቃት ስራ ተሰርቷል::  ሴት መምህራኑም ይህን የተፈጠረላቸውን አጋጠሚ ተጠቅመው በዛሬው መድረክ ላይ የምርምር ንድፈ ሀሳቦችን ማቅረብ መቻላቸው የሚበረታታና ቀጣይነቱም ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ 

በዩኒቨርሲቲው በሁሉም ዘርፍ የሚገኙ ሴት መምህርን ብቻ የምርምር ንድፈ ሀሳቦችን ያቀረቡበት በመሆኑ በአይነቱ ልዩና በዩኒቨርሲቲው ደረጃም ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ መሆኑን ፕሬዘዳንቷ ጠቁመው የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰቡ አገልግልት ም/ፕሬዝዳንት ፣ የምርምር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት እና በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሴቶችና ወጣቶች ፣ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ/ እና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ይህ መደረክ እንዲሳካ ላደረጉት ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በዚሁ መድረክ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልእክት ዩኒቨርሲቲው ወደ አፕላይድ ዩኒቨርሲቲነት እያደረገያለውን ሽግግር ሙሉ ለሙሉ ስኬታማ  ለማድረግ የሴት መምህራን ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡ ሴት መምህራንም ይህንን የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃት በመወጣት ጥረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የድሬደዋ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንትፊክ ዳይሬክተር አቶ ቴድርስ ገዳፋይ በበኩላቸው ሴት መምህራን በምርምር ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ከዚህ ቀደሙ በበለጠ አጠናክረው በመቀጠል የህብረተሰቡን ትክክለኛ ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገቡ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን በማበርከት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በውጤታማነት መፈፀም ይኖርባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡   


Share This News

Comment