Logo
News Photo

ዩኒቨርስቲ ልየታ የማፈጸሚያ ስትራተጂክ እቅድ እና በመጀመሪያ ድግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች ሊሰጥ የታሰበውን የመውጫ ፈተና/Exit exam/ በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለዩኒቨርስቲ አመራሮች እና ለተማሪ ተወካዮች ከትምህርት ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡

በዩኒቨርስቲው የትምህርት ጥራት ማጎልበትና የትምህርት ፕሮግራም ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ቢሮ አስተባባሪነት የተዘጋጀው መድረክ ላይ የእንኳን መጣችሁ ንግግር በማድረግ ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም ድሬድዋ ዩኒቨርስቲ በአፕላይድ ሳይንስ ከተመደቡት ዩኒቨርስቲዎች አንዱ እንደሆነ አስታውሰው ዩኒቨርስቲያችን ወደ እዚህ የሚያደርገውን ሽግግር የበለጠ ለማሳካት ከሁሉም የዩኒቨርስቲው አመራር ብዙ ስራ ይጠበቃል ብለዋል፡፡በማከልም ከመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ ም/ፕሬዝደንቱ እንደተናገሩት ት/ክፍሎችና የዩኒቨርስቲው መምህራኖች ከወዲሁ ራሳቸውን  ማዘጋጀት፤ ተማሪዎቻቸውን ለፈተናው ብቁ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ዝግጅት እና ጥረት ማደረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋ፡፡

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ሁባህ አደም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በተለይም ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ በዚህ ዙሪያ ኮሚቴ አዋቅሮ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመው ሂደቱንም የበለጠ ለማሳካት ለዩኒቨርስቲው አመራሮች እንዲህ አይነት መሰል መድረኮች ትልቅ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

ከመውጫ ፈተና ጋር አሰመልክቶ እንደተናገሩትም ሁሉም ተማሪዎቻችን በዚህ ፈተና እንዲያልፉ ማድረግ እንደሆነ ለሁሉም በመድረኩ ለተሳተፉት የዩኒቨርስቲው አመራሮች አቅጣጫ ሰተዋል፡፡ 

በመቀጠልም ከትምህርት ሚኒስቴር በመጡ ሁለት ባለሙያዎች በሁለቱም ርዕሶች ላይ ገለጻ የተደረገ ሲሆን ከዩኒቨርስቲ ልየታ ጋር ተያይዞ ልየታ ያስፈለገበት ምክንያት ፤ የልየታው መገምገሚያ ነጥቦች እንዲሁም እስካሁን በሚኒስቴር መስራቤቱ የተከናወኑ ሂደቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ የግንዛቤ ገለጻ የተደረገበት ሀሳብ በዩኒቨርስቲ ደረጃ ለሁሉም ተማሪዎች ከ2015ዓ.ም ጀምሮ ይተገበራል ተብሎ የታሰበው የመውጫ ፈተና አተገባበገር ላይ ሲሆን በመድረኩም የፈተናው አስፈላጊነት እና አይነት፤እንዴት እና መቼ እንደሚሰጥ፤ ምን ደረጃ ላይ የደረሱ ተማሪዎች እንደመወስዱት፤ስንት ጊዜ መውሰድ እንደሚቻል እና ተያያዥ ጉዳዩች ላይ ከባለሙያተኞቹ ገለጻ ከተደረገ በኋላ ከተሳታፊዎች እንዲብራራላቸው ባነሷቸው ሀሳቦች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

ለግማሽ ቀን በቆየው የውይይት መድረክ ሲጠናቀቅ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርስቲ ለመሆን የሚያደረገውን ጥረት በእያንዳንዱ መምህር እና ትምህርት ክፍል ላይ የወደቀ እንደሆነ አስረግጠው ያስረዱ ሲሆን ሁሉም ትምህርት ክፍል ለራሱ የሚሆነው ኢንደስትሪ ፈልጎ ከት/ክፍሉ ጋር በማስተሳሰር  ለተሞክሮ ለውውጥ ወደ ትኛውም ዩኒቨርስቲ መሄድ ሳያስፈልገን በድሬደዋና አካባቢዋ ያሉ ገጸ በረከቶችን ተጠቅመን የተሻለ አፕላይድ ዩኒቨርስቲ በመሆን እኛ ወደ ሌላ ዩኒቨርስቲ ሳይሆን ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ወደ እኛ ለተሞክሮ የሚመጡበት አንዲሆን ማድረግ ይቻላል በማለት ውይይቱን አጠቃለዋል፡፡


Share This News

Comment