Logo
News Photo

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ለ ፌደራል ፖሊስ አባላት ሲሰጥ የነበረው መሠረታዊ የኮንፒዩተር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

በስልጠናው መዝጊያ ላይ በዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ተማም አወል እንዳሉት ለደንበኞች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የፌደራል ፖሊስ ራሳቸውን ከዘመናዊ አሰራር ጋር ማላመድ የሚችሉበት ስልጠና መሰጠቱን በንግግራቸው አንስተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በድሬደዋ አስተዳደር ለሚገኙ የተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት መሠረታዊ የኮንፒዩተር እውቀት ማግኘት ችለው ስራቸውን በተቀላጠፈ ሁኔታ መከወን እንዲችሉ በተለያዩ ጊዚያት ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰው በቀጣይም የተለያዩ የስልጠና መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀት የሚሰጠውን ስልጠና ተጠናክረው የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ለ5 ተከታታይ ቀን በዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንት በመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀውን ስልጠና ተከታትለው ላጠናቀቁ የፌደራል ፖሊስ አባልት ከም/ፕሬዝዳንቱ ከዶ/ር ተማም አወል እጅ የእውቅና የምስክር ወረቀት ተረክበዋል፡፡

Share This News

Comment