Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዮኒቨርሲቲ በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የገጠር ሴት ተማሪዎች መኖሪያ/ሆስቴል ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በተለያየ ምክንያት የመከታተል ዕድል ያላገኙ ከድሬዳዋ ገጠር ቀበሌዎች የተውጣጡ ሴት ተማሪዎችን ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ መኖሪያ/ሆስቴል በማድረግ እያሰተማሩ ሲሆን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም በዛሬው እለት ለእነኝህ ተማሪዎች ምግብ-ነክና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡ 

ድጋፉን በቦታው ተገኝተው የተረከቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ እንዳሉት የተደረገው ድጋፍ ባጣም አስፈላጊ በሆነበት ሰዓት መሆኑን ጠቅሰው ዩኒቨርሲው ላደረገው ደጋፍ በሴት ተማሪዎች ስም አመስግነዋል፡፡ 

የተማሪዎቹ መኖሪያ/ሆስቴል አስተባባሪ ወ/ሮ አሚና መሐመድ ዩሱፉ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲውን አመስግነው በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶችም ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በድጋፍ እርክክቡ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ የኒቨርሲቲ የምህርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያደረገው ድጋፍ ተማሪዎቹ በምግብ ችግር ትምህርታቸው እንዳይስተጓጎልና ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩና በርትተው እንዲሰሩ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ሰለሞን አያይዘውም ከዚህ በፊት ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎቹ የማጣቀሻ መፅሀፍትንና የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ወንዲፍራው ደጀኔ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት ያደረገው ድጋፍ 38 ኩንታል ሩዝ፤50 ካርቶን ፓስታ፤ 150 አንሶላ፤ 50 አጎበር፤ ዘይትና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ተማሪዎቹ ባሉባቸው ችግሮች ሁሉ ዩኒቨርሲቲው ከጎናቸው እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

Share This News

Comment