Logo
News Photo

"ህግ ለሰብአዊ መብት ማስከበሪያና ለእድገት መሳሪያ ነው" በሚል ርዕስ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ 7ኛው የህግ ኮሌጅ ሀገራዊ የምርምር ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡

በኮንፈረንሱ መዝጊያ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በሀገራችን የዜጎች ሰብአዊ መብቶች ሙሉ ለሙሉ መከበር እንዲችሉ ህግን ተንተርሰው የሚሰሩ የጥናትና የምርምር ስራዎች  በስፋትና በጥራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡  

የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም በህጉ ዘርፍ ሰፊ ጥናትና ምርምር ከማድረግ ጎን ለጎ እርስ በእርስ የሚማማሩበትና ልምድ የሚቀስሙበት እንዲሁም የግንኙነት ትስስራቸው የሚያጠናክሩበት መድረክ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የአሁኑ አይነት ሀገራዊ የምርምር ኮንፈረንሶች መዘጋጀታቸው ያላቸው ፋይዳ የጎላ በመሆኑ ሳይቋረጡ ቀጣይነት ሊኖራቸው ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የህግ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ረ/ፕሮፌሰር አመንቲ አበራ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ሀገራዊ ኮንፈረንሱ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለ7ኛ ጊዜ በኮሌጅ ደረጃ ደግሞ ለ2ኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑን ገልፀው በኮንፈረንሱ ላይ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመጡ መምህራን አማካኝነት 11 የምርምር ስራዎች ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት እንደተደረገባቸውና በዚህም ጠቃሚ ልምዶች መገኘታቸውን አብረርተዋል፡፡

በመጨረሻም በኮንፈረንሱ ላይ በተጋባዝነት ለተገኙት የህግ ምሁርና ተመራማሪ ለዶ/ር ሰለሞን አባይ ፣ለምርምር ጽሁፍ አቅራቢዎች እና ለኮንፈረንሱ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካልት የእውቅናና የምስጋና የምስክር ወረቀት ሽልማት ከእለቱ የክብር እንግዳ ተበርክቶላቸዋለ፡፡


Share This News

Comment